Jump to content

እስክንድርያ

ከውክፔዲያ
እስክንድርያ
Ⲣⲁⲕⲟⲧⲉ Rakotə
የእስክንድሪያ ወደብ
ክፍላገር እስክንድርያ
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ 4,110,015
እስክንድርያ is located in ግብፅ
{{{alt}}}
እስክንድርያ

31°12′ ሰሜን ኬክሮስ እና 29°55′ ምሥራቅ ኬንትሮስ


እስክንድርያ ወይንም አሌክስዳንድርያ331 ዓክልበ.ታላቁ እስክንድርንግድ ማዕከል ለመሆን የተመሰረተች የጥንቱ ዘመን ታላቅ ከተማ ነበረች። በግብጽ አገር በግሪኮች የተመሰረተችው ይች የባህር ጠረፍ ከተማ በዘመኑ በምድር ላይ ከነበሩት ሁሉ ታላቅ የነበረውን የእስክንድርያ ቤተ መጻሕፍት በመያዝ ትታወቃለች። ስለሆነም ብዙ ስማቸው እስካሁን የሚጠሩ የግሪክ ተመራማሪዎች በዚች ከተማ ኖረዋል። ታዋቂው የጂዎሜትሪ ተማሪ ዩክሊድ በዚች ከተማ ይኖር እንደነበር ይጠቀሳል። በሌላ ጎን የጥንቱ ዘመን አለም አቀፍ አሰድናቂ የሚባለው የባህር ፋኖስ በዚሁ ከተማ ይኖር ነበር። እስክንድርያ፣ ከተቆረቆረ ጀምሮ ለሚቀጥሉት 1000 ዓመታት የግብፅ ዋና ከተማ በመሆን አገልግሏል። በኋላ ግብጽ በመስሊሞች ስትወረር ዋና ከተማው ወደ ፉስታት ካይሮ ተዛወረ።