BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
ቀጥታ, የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት እስራኤል ለሶማሊላንድ እውቅና መስጠቷን ተከትሎ አስቸኳይ ስብሰባ ጠራ
እስራኤል ከሶማሊያ ተነጥላ ነጻ አገርነቷን ላወጀችው ሶማሊላንድ ነጻ እና ሉዓላዊ አገርነት ዕውቅና ሰጥታለች። ይህ የእስራኤል ውሳኔ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ከሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት በመነጠል የነጻ አገርነት ዕውቅናን ስትጠብቅ ለቆየችው ሶማሊላንድ የመጀመሪያው የአገርነት ዕውቅና ነው። ነገር ግን ይህ የእስራኤል ዕውቅና የግዛቴ አለል ናት ከምትላት ከሶማሊያ ጀምሮ ከአፍሪካ ኅብረት፣ ከኢጋድ እና ከተለያዩ አገራት ጠንካራ ተቃውሞ ገጥሞታል።
እስራኤል ለሶማሊላንድ የነጻ እና ሉዓላዊ አገርነት ዕውቅና በይፋ ሰጠች
እስራኤል ከሶማሊያ ተነጥላ ነጻ አገርነቷን ላወጀችው ሶማሊላንድ "የነጻ እና ሉዓላዊ አገርነት" ዕውቅና መስጠቷን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታኒያሁ ይፋ አደረጉ። ይህ የእስራኤል ውሳኔ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ከሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት በመነጠል የነጻ አገርነት ዕውቅናን ስትጠብቅ ለቆየችው ሶማሊላንድን የመጀመሪያው የአገርነት እውቅና ነው።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል በሦስት የማዕድን ስፍራዎች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ሰባት ሰዎች ተገደሉ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በሚገኘው ቤሮ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ታጣቂዎች በሦስት የወርቅ እና የእምነበረድ ማውጫ ስፍራዎች ላይ በፈጸሙ ጥቃቶች ሰባት ሰዎች መገደላቸውን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ እና የፖሊስ አዛዥ ለቢቢሲ ተናገሩ። በዛሬው ዕለትም "በሌላ የማዕድን ስፍራ ላይ" የተኩስ ልውውጥ መደረጉን ተገልጿል።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, የሁለት መሪዎች ፉክክር እንዴት ፖለቲካዊ ቀውስ ፈጠረ?
ነጻነቷን ከተቀዳጀች ጥቂት ዓመታትን ያስቆጠረችው ደቡብ ሱዳን እስካሁን ዘላቂ ሰላም ለማስፈን አልቻለችም። ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና የቀድሞ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሪክ ማቻር የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ፤ መልሰው ወደ አለመግባባት ገቡ፤ በድጋሚ ወደ ክብ ጠረጴዛ አመሩ። በድጋሚ ውጥረቱ እየጨመረ ይገኛል። የሁለቱ መሪዎች ውሳኔ አገሪቱ ወደ መረጋጋት ሊያሸጋግር ካልሆነም አዲስ ቀውስ እንዲፈጠር ምክንያት ሊሆን ይችላል። ለመሆኑ በደቡብ ሱዳን ምን እየተካሄደ ነው?
ቪዲዮ, ስለስትሮክ ምን ያህል ያውቃሉ?
ስለስትሮክ ምን ያህል ያውቃሉ?
ቪዲዮ, ትራምፕ ሶማሊያውያን ላይ የሰነዘሩት አስተያየት የፈጠረው ስጋት
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ከካቢኔ አባሎቻቸው ጋር በነበራቸው ስብሰባ ላይ ሶማሊያውያንን ለይተው በሚያንቀሽሹ ቃላት ማጣጣላቸው መነጋገሪያ ሆኗል።
ቪዲዮ, ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል መሣሪያ ያነሱት የደቡብ አፍሪካ ሴቶች
በደቡብ አፍሪካ አሳሳቢ ከሆነው ፆታዊ ጥቃት ራሳቸውን ለመከላከል የጦር መሣሪያ አጠቃቀምን የሚለማመዱ ሴቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው።
ቪዲዮ, የሰውነት አካል የሚነግዱ ግለሰቦችን ያጋለጠው የቢቢሲ ምርመራ ዘገባ
በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ሴራ ሊዮን ከጥንቆላ ጋር ተያይዞ የሚደረግን ግድያ በተመለከተ ቢቢሲ ምሥጢራዊ የምርመራ ዘገባ ሠርቷል።
ቪዲዮ, ቻይናዊቷ ያጭበረበረችው 5 ቢሊዮን ፓውንድ ዕጣ ፈንታው ምን ይሆናል?
ቻይናዊቷ እንዴት ከ5 ቢሊዮን ፓወንድ በላይ በክሪፕቶከረንሲ ልታጭበረብር ቻለች? ይህ ገንዘብ በዩናይትድ ኪንግደም ታሪክ በፖሊስ የተያዘ ትልቁ የክሪፕቶከረንሲ መጠን ነው። በቻይና ስሙ ናኝቶ የነበረው የኦንላየን ኢንቨስትመንት በሦስት ዓመታት ውስጥ 128 ሺህ አባላትን አፍርቷል።
ቪዲዮ, ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ውይይት በማድረግ ላይ ለምን ተስፋ ቆረጠች?
ታላቁ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጋር "ተጨማሪ ውይይት" እንደማይደረግ የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብዲላቲ ተናግረዋል።
ቪዲዮ, "ቢገድሉኝ ይሻል ነበር'፡ የሴቶችን ሕይወት እያበላሸ ያለው የተዘነጋው የአማራ ክልል ጦርነት
ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው በአማራ ክልል በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚካሄደው ግጭት ሰላማዊ ሰዎች ከባድ ዋጋ እየከፈሉ ነው። ግጭቱ በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባሻገር በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እና ሰቆቃ ትኩረትን አላገኘም። ቢቢሲ ለወራት ባካሄደው ክትትል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶች የመደፈር እና የወሲባዊ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውን መረጃ አግኝቷል።
ቪዲዮ, አምስት ዓመት ያስቆጠረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ዳግም ይቀሰቀስ ይሆን?
በትግራይ የተካሄደው ጦርነት አምስት ዓመት ሆነው። ጦርነቱ ከፍተኛ ውድመት ከማስከተሉም በላይ ባለፉት አምስት ዓመታት በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ ክልል ውስጥ በርካታ ክስተቶችን ፈጥሯል። ጦርነቱን ያስቆመው የፕሪቶሪያው ግጭት የማቆም ስምምነት ባለፉት ሦስት ዓመታት አንጻራዊ ሰላም አምጥቷል። የሰላም ስምምነቱ ሦስተኛ ዓመት እየተዘከረ ባለበት በዚህ ወቅት የፌደራል መንግሥቱ እና ህወሓት እየተወነጃጀሉ ነው። ይህ መካሰስ ወደ ጦርነት ያመራ ይሆን?
አነጋጋሪ ጉዳይ
ኢትዮጵያ ወታደሮች እንድትልክ በአሜሪካ ተጠይቃለች የተባለለት የጋዛ ተልዕኮ ምንድን ነው?
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የጋዛን ጦርነት ለማስቆም ባቀረቡት የሰላም ሃሳብ ውስጥ የጋዛ ዓለም አቀፍ አረጋጊ የተባለ ኃይል የማሰማራት ዕቅድ አለ። በዚህም ከተለያዩ አገራት ወታደሮችን በማሰባሰብ በሚቀጥሉት ወራት ውስጥ ወደ ጋዛ ለማሰማራት አሜሪካ ጥድፊያ ላይ ናት። ኢትዮጵያም የዚህ ኃይል አካል እንድትሆን መጠየቋ ተዘግቧል። ይህ ኃይል ሐማስን ትጥቅ ማስፈተትን ጨምሮ የተለያዩ አላማዎች አሉት።
አዲሱ የንብረት ታክስ ረቂቅ ሕግ ከግብር ነጻ የሚሆን ቤተሰብን እንዴት ይለያል?
የገንዘብ ሚኒስቴር የንብረት ታክስ የሚጣልበትን እና የሚሰበሰብበትን መንገድ በተመለከተ ዝርዝር መረጃዎችን የያዘ "ሞዴል" ረቂቅ ሕግ በታኅሣሥ 2018 ዓ.ም. መጀመሪያ ወደ ክልል እና ከተማ አስተዳደሮች ልኳል። የንብረት ታክስን የመጣል እና የመሰብሰብ መብት የክልሎች ቢሆንም ከግብሩ ጋር ለሚያወጡት ሕግ "መነሻ የሚሆን ሞዴል" ረቂቅ ሕግ የሚዘጋጀው በፌደራል መንግሥት እንደሆነ የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ደብዳቤ ያስረዳል።
"ግብፅ ከኢትዮጵያ ጋር ችግር የለባትም፤ የምትፈልገው ሕጋዊ አስገዳጅ ስምምነት ላይ መድረስ ነው" - ፕሬዝዳንት አል ሲሲ
ግብፅ ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን በተመለከተ ከኢትዮጵያ ጋር ሕጋዊ አስገዳጅ ስምምነት ላይ ከመድረስ በስተቀር ሌላ ምንም ዓይነት "ችግር እንደሌለባት" ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ተናገሩ። ፕሬዝዳንቱ ይህንን የተናገሩት ግብፅ ውስጥ እየተካሄደ በሚገኘው ሁለተኛው የሩሲያ እና የአፍሪካ የትብብር መድረክ የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ካይሮ ከሚገኙ የአፍሪካ አገራት ልዑካን ጋር ባደረጉት ውይይት ላይ መሆኑ ተዘግቧል።
በ60 ቀናት አሜሪካን እንዲለቅቁ የተነገራቸው ኢትዮጵያዊያን ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል?
የአሜሪካ መንግሥት ከሦስት ዓመት በፊት ኢትዮጵያውያን በጊዜያዊ የሕግ ጥበቃ በአገሪቱ ውስጥ እንዲኖሩ የፈቀደበትን አሠራር እንዲያከትም ወስኗል። ላለፉት ዓመታት ለኢትዮጵያውያን ጥገኝነት ጠያቂዎች ሲሰጥ የነበረው ይህ ጊዜያዊ የሕግ ጥበቃ በመነሳቱ ከለላው የነበራቸው ኢትዮጵያውያን በሁለት ወራት ከአሜሪካ መውጣት ይጠበቅባቸዋል። ለመሆኑ የኢትዮጵያዊያኑ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ምን ሊሆን ይችላል? ምንስ አማራጭ አላቸው?
አደገኛው ታጣቂ ቡድን አይ ኤስ በምዕራቡ ዓለም ዳግም እየተጠናከረ ይሆን?
አይኤስ በመካከለኛው ምሥራቅ የነበረውን ድጋፍ እያጣ ከመጣ ወዲህ በአፍሪካ የተለያዩ አገራት ውስጥ እግሩን እያስገባ ነው። በምዕራብ አፍሪካ አገራት 12ሺህ የሚደርሱ ተዋጊዎች ያሉት አይኤስ በጎረቤት አገር ሶማሊያ ውስጥም ይንቀሳቀሳል። በዴሞክራቲክ ኮንጎ፣ በሞዛምቢክ እና ናይጄሪያም ቡድኑ እንቅስቃሴዎችን ያደርጋል።
ኤርትራ በድጋሚ ከኢጋድ ለመውጣት የወሰነችበት ምክንያት ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ ይሆን?
ኤርትራ ወደ ምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) አባልነት ተመልሳ ከገባች በኋላ ሦስት ዓመት ሳይሞላት ድጋሚ ከተቋሙ እራሷን ማግለሏን አስታውቃለች። ኤርትራ ከ20 ዓመታት በፊት ከቀጣናዊ ድርጅቱ የወጣችው ከኢትዮጵያ ጋር በነበራት ውዝግብ ውስጥ ኢጋድ ወገንተኝነት አለው በሚል ነበር። ኤርትራ የአሁኑ ውሳኔዋን ያሳወቀችው ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት በተበላሸበት ጊዜ መሆኑ ከድርጅቱ ለመውጣቷ ምክንያት ይሆን? የሚል ጥያቄን ፈጥሯል።
በቀይ ባሕር የጦር ሰፈር ለማቋቋም የተቃረበችው ሩሲያ ለቀጣናው ምን ይዛ ትመጣለች?
ከከተፎካካሪዎቿ ዘግይታ ወደ ቀይ ባሕር ወታደራዊ ኃይሏን ለማስፈር የተቃረበችው ሩሲያ በወሳኙ የባሕር መተላለፊያ ላይ ላይ አዲስ ኃይል ትሆናለች። በአፍሪካ የመጀመሪያዋን የባሕር ኃይል ጦር ሰፈር ለመመሥረት ስትጥር የቆየችው ሩሲያ አሁን ፍላጎቷን ዕውን ለማድረግ ተቃርባለች። ይህ የሩሲያ ኃይል ወደ ቀጣናው መምጣት ምን ይዞ ይመጣል?
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
ከየፈርጁ
ማርበርግ ቫይረስ: የመጀመሪያው ታማሚ እና ሦስት መሪዎቿን ያጣችው የጂንካ ቃለ ሕይወት ቤተ ክርስቲያን
ከሌሊት ወፎች የሚነሳው የማርበርግ ቫይረስ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ ከተገኘ አንድ ወር ሊደፍን ጥቂት ቀናት ቀርተውታል። የጤና ሚኒስቴር፤ እንዴት በሽታው በጂንካ ከተማ ሊነሳ እንደቻለ እስካሁን አልገለጸም። ለመሆኑ በጂንካ የመጀመሪያው ታማሚ ማን ነበር? የበሽታው መነሻ የሆኑት የሌሊት ወፎችን እና የመጀመሪያውን ታማሚስ ምን አገናኛቸው? ቢቢሲ ባደረጋቸው በርካታ ቃለ መጠይቆች ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ የሚሆኑ መረጃዎች አሰባስቧል።
'አሜሪካዊ ለመሆን ጫፍ ላይ እንደደረስን ነው ትራምፕ ዜግነታችንን የምንፈፅምበትን ሥነ ሥርዓት የሰረዙት'
በትራምፕ አስተዳደር የጉዞ እገዳ ከተጣለባቸው 19 አገራት ስደተኞች ዜግነታቸውን ለማግኘት ጫፍ ላይ ከደረሱ በኋላ የመጨረሻው ደረጃ ሥነ ሥርዓት እንደተሰረዘባቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አጃኢብ!
የአፋሩ እሳተ ገሞራ መቼ እንደሚፈነዳ ማወቅ ይቻል ነበር?
ሃይሊ ጉቢ እሳተ ገሞራ የፈነዳው ከ12ሺህ ዓመታት በኋላ ነው። እስከባለፈው እሑድ ድረስ አንዳችም እንቅስቃሴ ሳያሳይ ቆይቷል። የእሳተ ገሞራው አመድ በነፋስ አማካይነት አንድ ሺህ ጫማ ተጉዞ ጥቃቅን ቅንጣቶች ሰማይ ላይ ታይተዋል። ለመሆኑ ንቁ እሳተ ገሞራ እና ለዘብተኛ እሳተ ገሞራን ምን ይለያቸዋል? እሳተ ገሞራ ሊፈነዳ ሲል የሚያሳያቸው ምልክቶችስ የትኞቹ ናቸው?
የእስራኤል እና የኢራን ግጭት
አሜሪካ የ10 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት ያቀረበችበት የዋይት ሐውስ እንግዳ፡ አህመድ አል ሻራ
አዲሱ የሶሪያ ፕሬዝዳንት አህመድ አል ሻራ በአግባቡ የተተኮሰ ሱፍ ለብሰው፣ ፀጉራቸውን ወደ ኋላ አበጥረው ወደ ዓለም አቀፍ መድረክ ሲመጡ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንዳሉ ያስታውቃል። አሁን የትግል ልብሳቸውን ትተው፣ አዲስ ስም ይዘው በዓለም ላይ ካሉት በጣም ኃያላን መሪዎች ጋር ይጨባበጣሉ።
በመካከለኛው ምሥራቅ ኃያል የሆነችው የአይሁዶች አገር እስራኤል እንዴት ተመሠረተች?
በመካከለኛው ምሥራቅ ኃያል እና ብቸኛዋ የአይሁዶች አገር የሆነችው እስራኤል በዙሪያዋ ካሉ አገራት ሁሉ በዕድሜ ትንሿ ናት። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃት በኋላ በአውሮፓውያኑ 1948 የእስራኤል እንደ አገር መመሥረት በአካባቢው አሁን ድረስ እየተካሄደ ያለ ለውጥን አስከትሏል። ለመሆኑ በየዕለቱ የዓለም መገናኛ ብዙኃን ስሟን ሳያነሱ የማያልፏት ይህች አገር እንዴት ተመሠረተች?
እስራኤል 15 የጦር አውሮፕላኖችን አሰማርታ ኳታር ውስጥ የፈጸመችው ጥቃት
በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ ውስጥ እስራኤል ጥቃት የፈጸመችው በርካታ የሐማስ ፖለቲካ ቢሮ ባለሥልጣናት በሚኖሩበት የመኖሪያ አካባቢ ላይ ነው። በዚህ ጥቃት አስከ ስምንት የሚደርሱ ፍንዳታዎችን እና ከፍተኛ ጭስ በዶሃ ሰሜናዊ ክፍል ላይ ማየታቸውን ዓይን እማኞች ተናግረዋል። ከጥቃቱ ደቂቃዎች በኋላ ደግሞ እስራኤል ለተፈጸመው ጥቃት በይፋ ኃላፊነቱን ወስዳለች።
የእስራኤል ፕሬዝዳንት እንዲሆን ተጠይቆ የነበረው ታዋቂው የፊዚክስ ሊቅ አልበርት አንስታይን
የጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ቤን ጉርዮን መንግሥት በዓለም ታዋቂ የሆነው ሳይንቲስት አልበርት አንስታይን ለእስራኤል ፕሬዝዳንትነት እንዲሆን ካጩት በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ የእስራኤል አምባሳደር አባ ኢባን አንስታይንን እንዲያነጋግሩ ተደረገ።
ሐማስ በጋዛ ከሚደረገው ጦርነት ተርፎ ኅልውናው ሊቀጥል ይችላል?
ሁለት ዓመት ሊሞላው በተቃረበው ጦርነት በጋዛ ሰርጥ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሲገደሉ የግዛቲቱ አብዛኛው ክፍል ፈራርሷል። እስራኤል ዘመቻዋን ስትጀምር ያስቀመጠቻቸው ታጋቾችን የማስለቀቅ እና ሐማስን የመደምሰስ ዕቅዷ ከግቡ አልደረሰም። ከወዳጆቿ ሳይቀር ተቃውሞ ቢገጥማትም አሁን ደግሞ ጋዛን ሙሉ ለሙሉ የመቆጣጠር ዕቅድ እንዳላት ይፋ አድርጋለች። በርካታ መሪዎቹ የተገደሉበት ሐማስ ከዚህ ጦርነት በኋላ ዕጣ ፈንታው ምን ሊሆን ይችላል?
በእስራኤል ጥቃት እየተፈተኑ በሥልጣን ላይ አንድ ዓመት የሆናቸው የኢራኑ ፕሬዝዳንት
ማሱድ ፔዜሽኪያን ሐምሌ 2024 የኢራን ፕሬዝዳንት ሆነው ከተሾሙ ከአንድ ቀን በኋላ በቀጥታ ወደ ፖለቲካ እሳት ውስጥ ገብተዋል። ይህም አለመረጋጋት በሌለው በኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ መሪዎች ታሪክ ውስጥ ከታዩት ጅማሪዎች መካከል እጅግ አስደንጋጩ እና በቀውስ የታጀበ ነበር።
በአሜሪካ ድጋፍ የተጀመረው የኢራን የኒውክሌር ፕሮግራም ታሪክ
በአውሮፓውያኑ መጋቢት 5/1957 ዩናይትድ ስቴትስ በወቅቱ በመሐመድ ሬዛ ፓህላቪ ከምትመራው ኢራን ጋር ለሲቪል የአውቶሚክ ኢነርጂ አጠቃቀም የትብብር ስምምነት ተፈራረመች። በ'አተምስ ፎር ፒስ' መርሃ ግብር ጥላ ስር የነበረው ይህ ስምምነት የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር ለመጀመር መሠረት ጣለ። ለዋሽንግተን፣ በዚያ የቀዝቃዛ ጦርነት ወቅት ኢራን ተጨማሪ መስህብ ነበራት።
የተመለሱ ጥያቄዎች
"እናቴ መርዝ ልታበላኝ ስትል ደረስኩባት…" ሁላችንም ትንሽ ትንሽ 'እያበድን' ይሆን?
ስኪዞፍሪኒያ የሚባል የአእምሮ ጤና መታወክ እንዴት ያለ ነው? ፕሮፌሰር ሰለሞን ተፈራ ፒኤችዲ ሠርተውበታል። ለ20 ዓመት ተመራምረውበታል። በስኪዞፍሬኒያ የሚሰቃዩ በርካታ ታካሚዎች ነበሯቸው፤ አሏቸው። ፕሮፌሰሩ ነገርን በአጭር የማስረዳት ፀጋ አላቸው። ይህን የአእምሮ በሽታ እንዲህ ይገልጹታል። "ነገሩ የማርያምን ብቅል ሲፈጩ መዋል ነው" ይሉታል። ምን ማለታቸው ነው?
በሴቶች ላይ እየበረታ ከመጣው የማኅበራዊ ሚዲያ ጥቃት እንዴት ራስን መጠበቅ ይቻላል?
በዓለም አቀፍ ደረጃ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት እስከ 58 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች እና ልጃገረዶች በኦንላይን ለሚፈጸሙ ጥቃቶች ዒላማ መሆናቸውን የተባበሩት መንግሥታት የሴቶች ድርጅት አስታውቋል።
መጥፎ ጓደኛ ላለመሆን የሚረዱ አምስት ቀላል መንገዶች
እንዲኖረን የምንፈልገው ዓይነት ጓደኛ ለመሆን ማሻሻል ያለብን ባህሪዎች የትኞቹ ናቸው? እንዴትስ መጎ ጓደኛ መሆን ይቻላል? እነዚህ የብዙዎች ጥያቄ ናቸው።አንደኛው ጥሩ ጓደኛ መሆን የሚቻልበት መንገድ ተቃራኒ ማንነትን ማስወገድ ነው። ቋሚ መሆንን ጨምሮ በጎ ወዳጅ መሆን የሚቻልባቸውን መንገዶች እንመልከት።
በደቡብ ኢትዮጵያ ለሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ማርበርግ ቫይረስ መሆኑ ታወቀ፤ ክትባት ወይም መድኃኒት አለው?
በደቡብ ኢትዮጵያ በጂንካ ከተማ ተከስቶ ለስድስት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው በሽታ ማርበርግ ቫይረስ መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ። ከኢትዮጵያ በስተደቡብ በሚገኙ አገራት ውስጥ ተከስቶ የነበረው ይህ በሽታ ከሳምንት በፊት ነው በደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ተከስቶ ሁለት የጤና ባለሙያዎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎችን የገደለው።
ፎጣዎቻችን ለተለያዩ በሽታዎች ሊያጋልጡን እንደሚችሉ ያውቃሉ? እንዴት ንጽህናቸውን እንጠብቅ?
ሰውነታችንን አሊያም እጃችንን የምንደርቅባቸው ፎጣዎች ብዙ ጠቀሜታ ቢሰጡም እግረ መንገዳቸውን ረቂቅ ተህዋስያንን ከሰውነታችን ላይ ያነሳሉ።ፎጣዎቻችን ለምን ዓይነት በሽታዎች ያጋልጡናል? ፎጣዎችን ሳናጥብ ለምን ያህል ጊዜ እንጠቀምባቸዋለን? በምን ያህል ጊዜስ መታጠብ አለባቸወ?
ሌላ ዕይታ
ቢቢሲ አማርኛን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉ
ከማኅደራችን
"ቢገድሉኝ ይሻል ነበር"፡ የሴቶችን ሕይወት እያበላሸ ያለው የተዘነጋው የአማራ ክልል ጦርነት
ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው በአማራ ክልል በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በሚካሄደው ግጭት ሰላማዊ ሰዎች ከባድ ዋጋ እየከፈሉ ነው። ግጭቱ በሰው ሕይወት እና በንብረት ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባሻገር በሴቶች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እና ሰቆቃ ትኩረትን አላገኘም። ቢቢሲ ለወራት ባካሄደው ክትትል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴቶች የመደፈር እና የወሲባዊ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውን መረጃ አግኝቷል።
በብርሌ ፍቅር የወደቁት ፈረንጅ 'ብርሌ ውስጥ የኢትዮጵያ ታሪክ አለ' ይላሉ
ሰሞኑን አረቄ ብሔራዊ አጀንዳ ሆና የማኅበራዊ ሚዲያ አናት ላይ ወጥታ ነበር። ጠጅ ቢሆን አናት ላይ አይወጣም፤ ወደ ጉልበት ነው የሚወርደው። ጠጅ ለመጨረሻ ጊዜ ጉዳይ ሆኖ የሥነ መንግሥቱ አናት ላይ ወጥቶ፣ 'ብሔራዊ አጀንዳ' የነበረው በዐፄ ዮሐንስ 4ኛ ዘመን ነው። ድሮ ጠጅ በብርሌ ይቀርብ ነበር። ከዚያ በብርሌ ይጠጣ ጀመር። ጠጅ ግን እንደ አረቄ ማንም ‘ተራ ዜጋ’ ብድግ አድርጎ አያንደቀድቀውም።ብርሌ ውስጥ የመደብ ታሪክ አለ። የዘመን ታሪክ አለ። የጭሰኛና የመሳፍንት ታሪክ አለ። ያልተሳከረ።
ዓለምን የሚዞረው ኢትዮጵያዊ ከዩቲዩብ ምን ያህል ያገኛል?
ከተከፈተ በዚህ ወር 20 ዓመት የሆነው የቪዲዮ ማጋሪያው የማኅበራዊ ሚዲያ መድረክ ዩቲዩብ ለብዙዎች የተለያዩ አጋጣሚዎችን ፈጥሯል። ከእነዚህም መካከል አቤል ብርሃኑ አንዱ ነው፤ በዩቲዩብ አማካኝነት 62 ሀገራትን ዟሯል። ያልረገጠው አህጉር አንታርቲካን ብቻ ነው። ሁሉንም የአሜሪካ ግዛቶች አካሏል። ከዘጠኝ ዓመታት በላይ ዩቲዩብ ላይ የቆየው አቤል ከዩቲዩብ ምንያህል ያገኛል?
ቪዲዮ, በአርሰናል ‘ፍቅር የወደቁት’ የ65 ዓመቷ እናት፡ ወይዘሮ እቴቱ ማሞ, ርዝመት 3,29
ከእንግሊዝ ታላላቅ ቡድኖች መካከል አንዱ የሆነው የአርሰናል የልብ ደጋፊ የሆኑት ወ/ሮ እቴቱ ማሞ የ65 ዓመት እናት ናቸው። ላለፉት 20 ዓመታት አርሰናልን ያለማቋረጥ ደግፈዋል። እንደብዙዎቹ የቡድኑ ደጋፊዎች ዘንድሮ አርሰናል ዋንጫ ባለማንሳቱ ቢከፉም ድጋፋቸው ግን እንደሚቀጥል ይናገራሉ። ከሁሉም ተጫዋቾች ይልቅ እሳቸው ገብረኢየሱ ለሚሉት ለጋብሬል ጀሱስ እና ለቡካዮ ሳካ የተለየ ፍቅር አላቸው።
እነ ሞገስ አስገዶም፣ አብረሃ ደቦጭ፣ ፕ/ር አስራት ወልደየስ፣ ፕ/ር መስፍን ወ/ማሪያም፣ ስብሐት ገ/እግዚአብሔር የተማሩበት ተፈሪ መኰንን
ተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት ታሪክ የዘመናዊት ኢትዮጵያ ንድፍ እንደማለት ነው። ላለፉት 100 ዓመታት ታላላቅ ሰዎችን ወልዷል። ለመኾኑ ይህ ተማሪ ቤት እነማንን አፈራ? ይህ ሐተታ በ100 ዓመት ታሪኩ ውስጥ በአንድም ሆነ በሌላ አሻራቸውን ያሳረፉትን ግለሰቦች ያወሳል፤ ከካናዳዊያን ጄስዊቶች እስከ ከንቲባ አዳነች አበቤ፤ ከቱጃሩ ራስ ኃይሉ ተክለሃይማኖት እስከ ቢሊየነሩ ሼክ አላሙዲን፣ ከሐኪም ወርቅነህ እሸቴ እስከ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ።
ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት የምትገኘው አሊ ዶሮ እና አካባቢዋ ለምን የእገታ ማዕከል ሆኑ?
ባለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በሕዝብ እና በጭነት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች እና እገታዎች ተበራክተዋል። ይህ ክስተት ደግሞ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው የሰሜን ሸዋ አካባቢ በተደጋጋሚ ሲከሰት ቆይቷል። በተለይ አሊ ዶሮ የሚባለው ቦታ የጥቃት እና የእገታ ማዕከል ሆኗል እየተባለ ነው። ቢቢሲ በተለይ ይህ ቦታ ለምን የመንገደኞች እና የአሽከርካሪዎች ‘የሞት ቀጣና’ ሆነ? በሚል ለወራት የዘለቀ ምርመራ አድርጓል።
ባይተዋር ከተማ፡ “ፒያሳ፣ ካዛንቺስ... ሰፈሬ አልመስል አሉኝ”
ባለፉት ዓመታት በአዲስ አበባ በቅርስነት ተመዝግበው የነበሩ እንዲሁም ሌሎችም ታሪካዊ ሕንጻዎች፣ ቤቶች እና አካባቢዎች እንደ ዋዛ አፈር ለብሰዋል። በዚህ ዘገባ፣ አንድን ሕንጻ ወይም ቤት ቅርስ አልያም ታሪካዊ ሥፍራ ለማለት መስፈርቱ ምንድን ነው? የታሪካዊ ሕንጻዎች እና ቤቶች መፍረስ በታሪክ፣ በነዋሪዎች ሥነ ልቦና፣ በኪነ ሕንጻ እና በማኅበራዊ መስተጋብር ላይ ምን ጫና ያሳድራል? ቅርሶች እና ታሪካዊ ሥፍራዎችን እንዴት ጠብቆ ማደስ፣ ማዘመን፣ መልሰው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንዲሁም ከሌሎች ግንባታዎች ጋር ጎን ለጎን እንዲሄዱ ማድረግ ይቻላል? የሚሉት እና ተያያዥ ነጥቦች ተዳስሰዋል።
“ሰው መሃል ሆኜ ሁሉም ጨካኝ ሆኖብኝ ነበር” - የፀጋ በላቸው ዘጠኝ የጠለፋ ቀናት
ግንቦት 2015 ዓ.ም. የተፈጸመው የፀጋ በላቸው ጠለፋ ብዙዎችን ያስቆጣ፣ መነጋገሪያም የሆነ የወንጀል ድርጊት ነበር። ፀጋ፤ ከአንድ ዓመት ከመንፈቅ በፊት ተጠልፋ ያሳለፈቻቸውን ቀናት በተመለከተ ለመጀመሪያ ጊዜ ለቢቢሲ በዝርዝር ተናግራለች። ከቢቢሲ ጋር በነበራት ዘለግ ያለ ቆይታ፤ ስለተጠለፈችበት መንገድ እና ስላሳለፈቻቸው ዘጠኝ ቀናት በዝርዝር ተርካለች። ከጠለፋው ነጻ የወጣችበት መንገድም አስቀድሞ በክልሉ መንግሥት ከተገለጸው የተለየ እንደሆነ ለመጀመሪያ ጊዜ ተናግራለች። ለምን ከኢትዮጵያ እንደተሰደደች እና ስለ ቀጣይ ዕቅዶቿም እንዲሁ አጋርታለች።
". . . ከምድሩ ይልቅ የሰማዩን መንገድ ለመምረጥ ተገደናል" እገታ ያሰጋቸው መንገደኞች
ባለፉት ዓመታት በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ የሚካሄዱ ግጭቶች እና በታጣቂዎች የሚፈጸሙ እገታዎች ዜጎች በፈለጉት ጊዜ እና መንገድ በአገሪቱ ውስጥ እንዳይንቀሳቀሱ ብርቱ ስጋት ፈጥሮባቸዋል። በተለይ ደግሞ የመንገደኞች ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን በማድረግ የሚፈጸሙት ያላባሩ እገታዎች በዋነኞቹ የአገሪቱ ክልሎች ውስጥ እንቅስቃሴን አዳጋች አድርገውታል። በዚህም ሳቢያ አቅሙ ያላቸው እና የግድ የሆነባቸው ሰዎች ፊታዎችን ወደ አየር ትራንስፖርት አዙረዋል።
የአእምሮ ዕድገት መዛባት (ኦቲዝም) ያለባቸው መኪና እንዲያሽከረክሩ የሚረዳ ጥናት ለኳታር ያቀረቡት ኢትዮጵያዊ ተመራማሪ
ዛሬ፣መጋቢት 24 የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው። ይህ ዕለት በዓለም ደረጃ ታስቦ እንዲውል ለተባበሩት መንግሥታት ሐሳብ ያቀረበችው ኳታር ናት። ወደዚያው ብናቀና ዶክተር ወንድወሰን ግርማን እናገኛለን። ኦቲስቶች መኪና እንዲያሽከረክሩ የሚያስችል ከፍተኛ ምርምር ያደረጉ ኢትዮጵያዊ ናቸው።
'ዝምተኛው ገዳይ' በኢትዮጵያ
የዓለም ጤና ድርጅት የኢትዮጵያ የአየር ብክለት ልኬት ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል። ድርጅቱ እንደሚለው 99 በመቶው የዓለም ሕዝብ የሚተነፍሰው አየር ተበክሏል። ተላላፊ ላልሆኑ በሽታዎች የሚዳርገው የአየር ብክለት በኢትዮጵያ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ቢቢሲ ያነጋገራቸው ባለሙያ ይናገራሉ። ለመሆኑ በኢትዮጵያ ዋነኛ አየር በካዮች የትኞቹ ናቸው? መፍትሔውስ ምንድን ነው?













































































































