Jump to content

ዓፄ ተክለ ሃይማኖት

ከውክፔዲያ

ቀዳማዊ ተክለ ሃይማኖት፣ ዙፋን ስም ለዓለ ሰገድ፣ ከ1698 እስከ 1700 ዓም ድረስ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ነበሩ። የቀዳማዊ ዓፄ ኢያሱና የንግሥት መለኮታዊት ልጅ ነበሩ።

አፄ ኢያሱ ቁባታቸው ቅድሥተ ክርስቶስ አርፈው በጣና ሃይቅ ውስጥ ወዳለ ደሴት ቆይተው ነበር። በንግሥቲቱ መለኮታዊት ድጋፍ፣ ከመኳንንት ወገን አያሌዎች ኢያሱ እንደ ጥንቱ አክሱም ንጉሥ ካሌብ ማዕረቁን እንደ ተዉ ተከራከሩና ልጅ ተክለ ሃይማኖት በጎንደር እንደ ንጉሠ ነገሥት ሆነው ዘውድ ጫኑባቸው።

ይሄው ድርጊት በመላው ግዛት ስላልተቀበለ በተነሣው ሁከት ውስጥ ተክለ ሃይማኖት አባታቸውን ኢያሱን አስገደሏቸው። በዚህ ሥራ ስማቸውን «እርጉም ተክለሃይማኖት» አግኝተዋል።

በመስከረም ወር 1700 ዓም አንድ የጎጃም አመጸኛ እራሱን ንጉስ «ዓምደ ጽዮን አድርጎ አዋጀ። ወደ ዋና ከተማው በጎንደር ደርሶ ዘውድም ተጫነ። አጼ ተክለ ሃይማኖት ክረምት ቢሆንም ቶሎ ወደ ጎንደር ተመለሱ፤ ነጣቂውንም አባረሩት። ከትንሽ በኋላ ዓምደ ጽዮን በማይጻ በውግያ ተገደለ።[1]

ሆኖም ግን የተወደዱትን አባታቸውን ኢያሱን ስላስገደሉዋቸው፣ ሕዝቡ ለተክለሃይማኖት የነበረው ቅያሜ ጥልቅ ሆኖ ቀረ። እናታቸው መለኮታዊት እጃቸውን በነገሩ ስላስገቡ፣ ሌሎችም የንጉሣዊ ቤተሠብ አባላት ዝም ስላሉ፣ ይሄ ሁናቴ ለሥርወ መንግስቱ ክብርና ተጽእኖ ጉዳት ሆነ። ሎሌዎቻቸው በሤራ ይገቡባቸው ጀመርና የሥርወ መንግሥቱ ዋጋ ምን ያህል እንደ ነበር የሚሉ ውይይቶች በዙ።

በአገር ቤት እየተጓዙ አጼ ተክለሃይማኖት በአባታቸው ሎሌዎች ዕጅ በጩቤ ተወግተው ዓረፉ።[2]

በአንዳንድ የታሪክ ምሁራን አስተሳሰብ፣ የኢትዮጵያ ዘመነ መሳፍንት የጀመረበት ድርጊት ያው ኢያሱ በልጃቸው ተክለሃይማኖት ትዕዛዝ ሲገደሉና ከዚያ የሥርወ መንግሥቱ ክብር ሲዋረድ ተከሠተ ብለው ያምናሉ።

  1. ^ E.A. Wallis Budge, A History of Ethiopia: Nubia and Abyssinia (1928) (Oosterhout, the Netherlands: Anthropological Publications, 1970), p. 425f
  2. ^ Pankhurst, Richard K. P. (1982). History of Ethiopian Towns. Wiesbaden: Franz Steiner Verlag. pp. 142f. ስኮትላንድ ተጓዥ አቶ ጄምስ ብሩስም እንደ ጻፉት፣ እያደኑ ሁለት የአባታቸው ሎሌዎች ገደሏቸው (Travels to Discover the Source of the Nile [1805 edition], vol. 4 p. 14f.)

ቀዳሚው
ቀዳማዊ ዓፄ ኢያሱ
የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት
1698-1700 ዓም
ተከታይ
ዓፄ ቴዎፍሎስ